ቀዳሚ ገጽ » » ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል: አስተዳደራዊ ችግሮችና የወደፊት ስጋቶች ተናግረዋል

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል: አስተዳደራዊ ችግሮችና የወደፊት ስጋቶች ተናግረዋል

Written By bahir dar city foot ball club on Wednesday, April 1, 2015 | 11:25 PM

(haratewahdo)ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንሊቀ ጳጳስ፣የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር እና ልማት ድርጅትየበላይ ሓላፊ *.እኛ ዘንድ ቀኖና እና ሥርዐት ሲጣስ ‘No’ ማለት የለም፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ማስፈጸምከኹሉም የሥራ ሓላፊዎች የሚጠበቅ ኾኖ ሳለበዝምታ ማየት ነው፡፡ ምእመናን ናቸውሃይማኖታችንእያሉ የበለጠ መቆርቆር እያሳዩ ያሉት፡፡ *.መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ በየጊዜው በሚፈጠረው ውዝግብ የተነሣ÷ የቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖናዊ ሥርዐት ይጣሳል፤ የእርስ በርስ ግጭት ይስፋፋል፤ ሙስናና ዝርፊያ ይንሰራፋል፤ ገጽታዋ ይዳከማል፤ ኢኮኖሚያዊ አቅሟ ይቀንሳል፤ የሕዝብ ድጋፍ እና የውጭ ዕውቅና ይጠፋል፤ የውስጥና የውጭ ጠላቶቿ ይበረታሉ፤ አንድነቷ ተናግቶ በየመንደሩ ልዩ ልዩ እምነቶች ይፈጠራሉ፤ በመጨረሻም መበታተን እና መከፋፈል ይከተላል፡፡ *.ልቅ ዝርፊያና ሙስና፣ መንፈሳዊነት እና ሰብአዊነት የሌለው መሥመር የለቀቀ ዘረኝነት፣ የፋይናንስ ሥርዐቱን እና የንብረት አያያዙን የሚያዘምን አስተዳደራዊ ሥርዐት እንዳይኖር ከሚቃወም የአመለካከትና የተግባር ድክመታችን መላቀቅ ይገባናል፡፡ ወቅቱን የዋጁ፣ በተግባር የሚተረጎሙ ሕገጋት እና ደንቦች ያስፈልጉናል፤ በረጅምና በአጭር ጊዜ ዕቅዶች መመራት ይኖርብናል፤ዕውቀትን መሠረት ያደረገ፣ በተሰጠው ሓላፊነት የሚጠየቅ፣ በማያቋርጥ ሥልጠና አቅሙን የሚገነባየሰው ኃይል ምደባና ሥምሪት ያስፈልገናል፡፡ *.በታሪካቸው ከእነሐርቫርድ የሚወዳደሩ እና የሚልቁ የአብነት ት/ቤቶቻችን ሥርዐተ ትምህርት ከወቅቱ አንጻር ማደራጀት እና በየክልሎቹ ማስፋፋት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችንን ምሩቃን እንደ የክህሎታቸው በሥልጠና ማብቃት፣ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንት እና ምሁራን በአግባቡ ማሳተፍና መጠቀም ይጠበቅብናል፡፡ ብፁዕነታቸው፣በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ማእከልግብዣ፣‹‹ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች እና መፍትሔዎች››በሚል ርእስ ትላንት ማምሻውን በመንፈሳዊ ኮሌጁ አዳራሽ በርካታ ተከታታዮች በተገኙበት ያቀረቡትን የውይይት መነሻ ሐሳብ(public lecture)ሙሉ ይዘት ይከታተሉ፡፡

0 አስተያቶች:

Post a Comment

Facebook Twitter Addthis Google+