ቀዳሚ ገጽ » » ትንሳኤን በበረከት ከፍኖተ ሕይወት

ትንሳኤን በበረከት ከፍኖተ ሕይወት

Written By bahir dar city foot ball club on Wednesday, April 1, 2015 | 12:13 PM



አንባብያን ሆይ እስኪ እራሳችን ከዚህች በታች ያለችውን ጥያቄወች እንጠይቅ ።

v  በዓልን እንዴት ላሳልፍ አስቤአለሁ ?
v  እስካሁን እንዴት እያሳለፍኩ ነው
v  እራሳቸውን መጦር ላልቻሉ ወገኖቻችን እኔ ያገባኛል ?
አወ ሁሌም እራሳችን በጠየቅን ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባን ኅሊናችን እራሱ ይነግረናል ብዙወቻችን በዓልን ማሳለፍን ስናስብ ሥጋዊ ደስታችን አሰብን ነው በዓላት ላይ ግን ከስጋችንም በላይ ነፍሳችን ልትደሰት ትወዳለች ሥጋ በመብል እንዲደሰት ነፍስ ደግሞ በምንሰራው ትሩፋት ትደሰታለች ጠጥተን ስጋችን እንድናረካ ነፍሳችንም የነፍስ መጠጥ የሆነውም ደካሞችን በመርዳት ነፍሳችንን ከጥ አርክተን በበዓሉ እንድናስደስታት ትፈልጋለች
ትንሣኤው ከስጋ በላይ የነፍስ ደስታዋ ነውና ስለትንሣኤ ለስጋ ከመደብንላት ደስታም በላይ ለነፍሳችን በመመደብ እናስደስታት ዘንድ ይፈለጋል ። ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅም ስለ ምጽዋት እንዲ   ያስተምረናል
"እስመ ምጽዋትሰ ምግባር ትርፍት ይእቲ ።
ምጽዋት ፍጹም ስራ ናት
ወተኖላዊት ይእቲ ለገባሪሃ ።
ለሚሰራም ሰው ጠባቂው ናት
ወፍቅርት ፈድፋደ በኀበ እግዚአብሔር ልዑል ።
በልዑል እግዚአብሐየር ዘንድ የተወደደች ናት
ወተንባሊት ይእቲ ለዘይፈቅድ ደፀያሕ መፍቅጹ ።
ሥራውም ይከናወን ዘንድ ሚወድ ሰው አማላጂ ናት"
ተግሳጽ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርስ ክርስቶስ
ባህር ዳር ላይ መቀመጫውን ያደረገው የ ደ/ቅ/አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤትም የሰወችን የሥጋ ርሐብ በማስታገስ የራሳችንን ነፍስ እናጠግብ ዘንድ ዘወትር በየዓመቱ በሚያከናውነው የነዳያን እና የአገልጋይ ካህናት የማግደፍ መርሐግብር ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ጥሪውን ያስተላፋል
በየትኛውም መልኩ ለማግደፊያው አስተዋጽኦ ማድረግ እምትፈልጉ ምዕመናን ይህንን አድራሻ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን
     በ አዲስ አበባ የምትገኙ  
v  0918008905
v  0933566509
v  0933735529
ባህር ዳር እና አካባቢው
v  0918716590
v  0918718257
ይደውሉልን በመርሐግብሩም ለመሳተፍ እምትፈልጉ በዕለቱ ከቅዳሴ በላ በ ሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ መገኘትእምተችሉ መሆኑን እናሳውቃለን
ትንሳኤው የስጋ ብቻ ሳይሆን የነፍሳችንም መደሰቻ ያድርግልን በያለንበት አካባቢ ነዳያንን እናግድፍ አንድ ላለን ለሌለው እናድርስ ህሙማንን እንጠይቅ ፍቅርን እንለግሳቸው

          ሰ/ት/ቤቱ

0 አስተያቶች:

Post a Comment

Facebook Twitter Addthis Google+