ቀዳሚ ገጽ » » አገልግሎትን ለመስጠት ከመንፈሳዊነታችሁ አትቀንሱ

አገልግሎትን ለመስጠት ከመንፈሳዊነታችሁ አትቀንሱ

Written By bahir dar city foot ball club on Wednesday, March 18, 2015 | 9:32 AM


Ø  ቅዱስ ጳውሎስለትምህርትህከማለቱ በፊትለራስህማለቱን አስተውሉ እርሱ ይህንንያለው ይህ ጉዳይ ለድኅነቱና የሚናገረውን ቃል ለሚሰሙት ሰወች ድኅነት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።

Ø   እነዚህ ሰወች አገልግሎት ገጽታ አላቸው እንጂ ውስጣቸው ጠፍቷል   ከእነዚህ ሰወች አንዳንዶቹ ስለራሳቸው የሚያስቡ ነበሩ ይሁን እንጂ አገልግሎትን ሲጀምሩ ቸልተኝነት በልቦናቸው ውስጥ ዘልቆ ይገባል
Ø  ሰወች ራቸውን በመርሳት በአገልግሎት ውስጥ ቢታገሉ መንግስተ ሰማያትን ከማጣት በስተቀር የሚጠቀሙት ጥቅም ምንድን ነው ?
Ø  እንዲህ አይነቱ ሰው ግን ሊያውቀው የሚገባ ትልቁ ጠቃሚ እውነት ቢኖር ወደ እግዚአብሔር ሚመራው አገልግሎት ሳይሆን ንጹህ ልብ መሆኑን ነው

 “ለራህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ በእነዚህም ጽና ይህንን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙትንም ታድናለህ. . .” 1 ጢሞ 416
    ታላቁ ሰባኪ ቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎትን በጥልቀት ተግባራዊ አድርጓል መንፈሳዊ ሕይወትን በሚገባ ተለማምዷል ፤ከሌሎች ሐዋርያት ይበልጥም እጅግ ደክሟል (1 ቆሮ 1510)
   ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ቃል የጻፈው በኤፌሶን ጳጳስ ለነበረው ለደቀ መዝሙሩ ጢሞቲወስ ነው። ጢሞቲወስ  ትክክለኛውን ዕምነት መጀመርያ የተማረው ከአያቱ ከዚያም ከእናቱ ኋላም ከቤተሰቦቹ ስለነበር ከሕጻንነቱ አንስቶ ቅዱሳት መጻህፍትን ያውቅ ነበር
  መምህሩ ቅዱስ ጳውሎስለራህ ተጠንቀቅ . . . ” በማለት የተናገረው ቃል ልብ በሉ እርሱ ይህን የተናገረው አገልግሎት መስጠት ቀላል ባልሆነበት በኤፌሶን ከተማ ውስጥ ጵጵስናን ታላላቅ ሸክሞች ኀላፊነቶች መወጣት ከባድ ስለነበረ ነው እራሱ ቅዱስ ጳውሎስምእንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልኩ . . . ” (1 ቆሮ 1532) በማለት ተናግፘል።
   ቅዱስ ጳውሎስለትምህርትህከማለቱ በፊትለራስህማለቱን አስተውሉ እርሱ ይህንን ያለው ይህ ጉዳይ ለድኅነቱና የሚናገረውን ቃል ለሚሰሙት ሰወች ድኅነት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።
   አንድ ሐዋርያ ከአገልጋዮችም ሆነ ከምዕመናን ጋር መተዋወቁ መሰረታዊ መመርያ ነው አገልጋዮች ማንነታቸው ይበልጥ የሚታወቀው በዚህ ነውና ግን ለምን ?
ለራስህም ተጠንቀቅ..ለምን ?
     ዚህ ምክንያት ከፍተኛ የዝና እንቅስቃሴ እንዲሁም ለሌሎች ሰወች የማሰብ ደረጃ ላይ የደረሱና ስሞቻቸው ታዋቂ የሆኑላቸው ሰወች ራሳቸውን በመዘንጋታቸው ስለጠፉ ነው
    እነዚህ ሰወች አገልግሎት ገጽታ አላቸው እንጂ ውስጣቸው ጠፍቷል
  ከእነዚህ ሰወች አንዳንዶቹ ስለራሳቸው የሚያስቡ ነበሩ ይሁን እንጂ አገልግሎትን ሲጀምሩ ቸልተኝነት በልቦናቸው ውስጥ ዘልቆ ይገባል እነዚህ ሰወች ስለሌላ ሰወች በማሰባቸው እንጂ ስለራሳቸው ባለማሰባቸው ተልዕኮአቸውን እንዳጠናቀቁ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል አንዳንዶቹ ደግሞ ከሚያስተምፘቸው ህጻናት ወይም ደቀ መዛሙርት እጅግ ዝቅ ባለ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ሐዋርያው ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸውለራስህ ለትምሕርት ተጠንቀቅ ይላቸዋል. . .”   ለምን ?
    “ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይተርፈዋል . . . ?” (ማቴ 1626)
    ሰወች ራቸውን በመርሳት በአገልግሎት ውስጥ ቢታገሉ መንግስተ ሰማያትን ከማጣት በስተቀር የሚጠቀሙት ጥቅም ምንድን ነው ? እያንዳንዳቸው ራሄልን እንደወሰዱ ቢያስቡም የወሰዱት ግን ልያን ነው ብዙ አገልጋዮች በአገልግት ውስጥ ሳሉ ከዚህ ቀደም ያልተቸገሩባቸው የተለያዩ ችግሮች ጠቦች ውግዘቶች ወደ ሕይወታቸው መግባቱን ይደርሱበታል
   እውነቱን ለመናገር ግን አገልግሎት የእነዚህ ችግሮችና ጠቦች መገኛ ምክንያት አይደለም ይሁን እንጂ ለራሱ የማይጠነቀቅ ሰው በእነዚህ ጉዳዮች ጉዳት ሊደርስበት ይችላል እርሱ በአገልግሎት ውስጥ ብዙ ስህተት ላይ ሊወድቅ ይችላል እርሱ ፈጽሞ ያልተገነዘባቸው አዳዲስ ኃጢአቶች ይከሰታሉ ወይም ተሸሽገው ከቆዩ በኋላ አሁን ይገለጣሉ
   እርሱ አውቆትም ይሁን ሳያውቀው አገልግሎት ከፍ አድርጎ ያሳደገው ቢመስለውም እርግጡ እውነት ግን ቁልቁል መውረዱ ወይም መውደቁ ነው
    እርሱ በአገልግሎት እያደገ ሲሄድ ተካፋይ ሚሆንባቸው ነገሮች እያደጉ ስለሚሄዱ ስህተቶቹም እያደጉ ይሄዳሉ ኃላፊነቶቹ እየጨመሩ ሲሄዱም ሙሉ ጊዜው ይዋጣል ራሱን እስከመርሳትም ይደርሳል እርሱ ለነፍሱ የሚያስፈልጋትን ምግብ ስለማያቀርብላት ቁልቁል ይወድቃል አገልግሎቱን በማቆም ለራሱ እንዲጠነቀቅ ምክር ብትሰጡትም እጅግ ያዝናል ።አልግሎት ለእርሱ ሁሉ ነገሩ ስለሆነ ያለ እርሱ ሊኖር አያችልም እንዲህ አይነቱ ሰው ግን ሊያውቀው የሚገባ ትልቁ ጠቃሚ እውነት ቢኖር
    ወደ እግዚአብሔር ሚመራው አገልግሎት ሳይሆን ንጹህ ልብ መሆኑን ነው
እውነተኛ አገልግሎት አንድን ሰው መንፈሳዊነት ቀንሶ እስከሚጠፋ ድረስ ሊገኝ አይችልም ሰውየው ለራሱ የሚገባውን እንክብካቤ ሊያደርግ አልቻለምና እርሱ  “ . . . እግዚአብሄ መንግስት በመካከላችሁ ናትና . . .” ( ሉቃ 1721) ሚለውን ቃል ስለሚዘነጋና ሙሉ ትኩረቱን በውጪያዊው ጉዳይ ላይ ብቻ ስለሚያደርግ እግዚአብሔር መንግስት ከውጪ በህዝቡ መካከል እንዳለች አድርጎ ያስባል !
   አንድ አንድ አገልጋዮች በፒራሚድ ሚመሰል መንፈሳዊ ሕይወት ስላላቸው ለራህ ተጠንቀቅ እነርሱ በመጀመርያ እስከ ጫፍ ድረስ ወጥተው በኋላ ቁልቁል ይወርዳሉና
   እንደዚህ አይነቶቹ አገልጋዮች ጊዜ ቢኖራቸውም ጊዜ የእነርሱ አይደለም ከዚህ በተጨማሪ ትኩረታቸውምስሜቶቻቸውም የእነርሱ አይደሉም። ሁሉም ጊዜ እንክብካቤ ስሜቶቻቸው የተሰጡት እነርሱአገልግሎትብለው ለሚጠሩት ጉዳያቸው ነው። እነርሱን መንፈሳዊነት በተመለከተ ግን ምንም አይነት ጊዜ ሊያገኙ አይችሉም በልባቸውም ውስጥ ለዚህ ጉዳይ ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም ! አንዳንዶች ይህንን የሚቆጥሩት ለሌሎች መስዋዕት እንደሞህን አድርገው ነው!!
     የራስ መስዋዕትነት የቅድስና ስራ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ይሁንና የራስን መንፈሳዊነት መስዋዕት ማድረግ ግን ኃጢአትም ጥፋትም ነው በአንድ ወቅት መጥምቁ ዩሀንስእርሱ ሲልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል ”(ዮሀ 330) በማለት ተናግሯል እርሱ ይህንን ሲናገር በመንፈሳዊነት ወይም በእግዚአብሔር ፍቅር ፈጽሞ ለማነስ አይደለም ይህንን ለማለት ፈልጎ አይደለም !!  እርሱ ለማነስ የፈለገው በክብር በአገልግሎትና በዝና ነው ከዚህ በተቃራኒ የእርሱ መንፈሳዊነት የሚጨምረው በቦታው ላይ ክርስቶስ ራሱ ቤተክርስትያንን እንዲመራና ሙሽራይቱን እንዲቀበል ቦታን ሲለቅ ነው በእርግጥም መጥምቁ ዩሀንስ ያነሰ ይምሰል እንጂ ጨምሯል አርሱ የጨመረው በትሕትና በእግዚአብሔር ፍቅር በክርስቶስ ላይ ባለው ዕምነትና በጌታ ስራ ላይ ነው።
     ለራችሁ ተጠንቀቁ ! በአገልግሎት ውስጥ እያላችሁ መንሳዊነታችሁ ከቀነሰም ራችሁን ለማደን አንድ ርምጃ ተራመዱ
     አገልግሎትን ለመስጠት ከመንፈሳዊነታችሁ አትቀንሱ ስለመንፈሳዊነታችሁም ስትሉ አገልግሎታችሁን አታቁሙ ይልቁንም ከባከነ ጊዜአችሁ በመቆጠብ ለመንፈሳዊነታችሁ ለግሱ ዓለማዊ  ተከፋይነታችሁን በመቁረጥ መንፈሳዊነታችሁን ተንከባከቡ። ከቸልተኝነታችሁ በመንቃት የአገልግሎትን እውነተኛ አሰራር ተረዱ አገልግሎት የት እንዳላችሁ ሳታውቁ የምትሽከረከሩበት አዙሪት አይደለም።

                ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

               /spiritual ministry & spiritual minister/

 

0 አስተያቶች:

Post a Comment

Facebook Twitter Addthis Google+