ቀዳሚ ገጽ » » ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን እሱን አትንኩብን ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳንና ኤርምያሳውያን

ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን እሱን አትንኩብን ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳንና ኤርምያሳውያን

Written By bahir dar city foot ball club on Friday, March 20, 2015 | 9:19 AM

እሱን አትንኩብን እሱን ስትነኩት ንቦቹ ከቀፎው ይለቀቃሉ
….
ዳኒ(ሙኃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ይህንን ስም ዳኒ ብይ ስጠራ ከፍቅር እንጂ አክብሮትን ከማሳጣት እንዳይወሰድብኝ)  በብሎጉ ላይ አንድ ጹሁፍ ይጽፍና በጣም የወደድኩትን አንቀጽ አውጥቸ ኮሜንት አደረጋለሁ አንቀጹ ምንም ሳያቁ ስለሚጽፉ ጸሐፊያንና መምህራን ነበር ።
ያንን የተመለከተና ሙሉውን ጽሁፍ ያላነበበ ወንድሜ  ግን የውስጥ መልእክት ላይ "አንተም እነሱን ሰምተሕ ተለወጥክ ? እንዲያውስ ዋናው አንባቢ አንተ አልነበርክምን ? እጂግ በጣም አዝኛለሁ አለኝ ።" መጀመርያ ስላልገባኝ ደነገጥኩ ከዛ ግን አስረዳሁት ተግባባን ግን መጨረሻ ላይ ግራ እንደገባው ነግሮኝ ምን ጣስባለሕ አለኝ ? ሁለተኛ ሰው ስለዚሕ ሲደግመኝ ግን ገረመኝና ደግሜ ጽሁፉን አነበብኩት እውነት ለመናገር ከጭፍን ደጋፊነት የዘለለ መልስ ለመጻፍ እንኳ እማይሆን ተራ ጽሁፍ ነው ። ምን ሰማሁና ልለወጥ ?
ሰው ከተለያዩ ነገሮች ተነስቶ አንድ በተለያየ መንገድ  ታዋቂ የሆነን ሰው ይቃወማል
1.  ከትክክለኛ የሰውየው ስሕተት በመነሳት
2.  አንድ ያሰው የሰራውን ስራ አይቶ በመናደድ ከስሜታዊነት በመነሳት
3.  አንድ ሰው ከኔ የተሸለ ስራ ሰርቷል ብሎ ማጣጣል እበልጣለሁ ብሎ ከማሰብ
4.  እምወደውን ነገር አካል ሰው ተናግሯል እና እኔም ልናገረው ከሚል እና ከተለያዩ ምክንያቶች
እኔ የሰሞኑን ከ ዳኒ ጋር የተነሱ ተቃውሞወችን እማያይዘው የመጀመርያውን የ አ/ቶ ኤርምያስን አላቅም ምክንያቱም ከብዙ አመት በኋላ ከእንቅልፍ ገና እንደነቃ ሰው ተነስቶ የጻፈን ሰው ምን ይባላል "ደሕና አደርክ " ማለት ነው እንጂ የሰዓሊውን ግን ያው ከ ዓራተኛው እመድበዋለሁ እናንተ አንብባችሁ ከምትመድቡት መድቡት ።
ምንም ያለምክንያት የተጻፈ ተራ ጹሁፍ ከርዕስ የዘለለ ምክንያዊነት የሌለው ጽህፍ ሊረብሸንም ሊያስገርመንም አይገባም አንድ ነገር እኮ ሊረብሽም ሊታመንም እሚገባው ቁም ነገር ያለውና  ምክንያታዊ ሲሆን ነው ። ዓረፍተ ነገር ለማሳመርማ እኮ ትንሽ ማንበብ እንጂ ምክንያት አያስፈልግም ።
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ሆይ ማንነትክን ስለማላቅ ዓላማህን መንገር ባልችልም ኤርምያሳዊነት ሙከራህ ተሳክቶልሃል ትንሽም ቢሆን እረብሸሀልና እስኪ ከቻልክ አንተም ወረድ ብለህ የጻፍከውን አንብበው አንተም ይገርምሐል  በ "ይመስለኛል" እየጻፍክ ይህን ያክል ?  ነገሩ አንተ ምን ታደርግ ያገኙትን እሚለቁት ብሎጎች እንጂ ጥፋተኞቹ።
አንባብያን ሆይ እስኪ ይህ ጽሁፍ መሬት እማይነካ ተራ ተቃውሞ መሆኑን ለማሳየት እንዲ አዘጋጅቸዋለሁ እንደ መልስ አታስቡት ይህ የግል እይታየ ብቻ ነው ። ገፍቶ የመጣን እማ አስታጥቀው እሚጭኑ ብዙወች አሉ።
በቀይ ከለር የተቀመጡት ሰዓሊው በጸሀፊነት ከጻፉት ጽሁፍ የተወሰደ ነው ።

Ø   / ዳንኤል ክብረትና አቶ ውብእሸት ወርቅ አለማሁ ከአገዛዙ የተሰጣቸውን ተልእኮ ለመወጣት / ዳንኤል እኛኢትዮጵያዊያን ብንበላው የማንጨርሰው ሀብት ያለን ስለሆነ በፍጹም መሰደድ እንደሌለብን ይናገራል
    ቆይ የሰው መሰደድን መቃወም ምኑ ላይ ነው ክፋቱ አይደለም ሌላው ተሰዳጆቹ ወገኖቻችን እኮ ፈልገው አልተሰደዱም አሁንስ ቢሆን ኢትዮጵያ ለሕዝቦቹዋ እሚሆን የራሱዋ ነገር የራሱዋ ጥበብ በእውኑ አጣለችን ?  እንዴ ሰው ሁሉ ዛሬ በሐገሬ አልተመቸኝም ብሎ ወጦ ካለቀ ነገ ሙሉ ሆኖ እችን ሐገር እሚረከበው የትኛው ዜጋ ነው ? አባቶቻችን ትላንት ወጠው  አልቀው ቢሆን እኮ ዛሬ ታሪካ አልባ ሐገር ሆነን ነበር ? ታድያ ሰው ሁሉ ተሰዶ ነገ ለዚህች ሐገር ዜጎች ምን ይቆያቸው ? ሐገር እኮ ሐገር እምትባለው ሰው ሲኖርባት ብቻ ነው ። ማንም ስደትን እሚደግፍ እሱ ነው የሐገር ጠላት። እና ስደትን በተቃወመ ? ነው ወይስ እንደ ብዙወች መውጫውን አመቻችቶ ስለ መንግስት ተቃውሞውን  ተናግሮ (የውጩን ኖሮ ለማሳመር) ስደትን መምረጥ እና መደገፍ አለበት ?
Ø  በመጽሐፍ ደረጃ ፀረ ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያን የሆነ ጽሑፍ የሌለውን ፍለጋ 
ይህን ጽሁፍ አንባብያን ሆይ ዳኒ በሁለት ክፍል አዘጋጅቶ ያቀረበው ጽሁፍ ነው ዳኝነቱን ለእናንተ በሎጉ ላይ  ክፍል አንድን (Tuesday, October 29, 2013) ክፍል ሁለቱን (Tuesday, November 5, 2013) ጽሁፍ ላይ ታገኙታላቹ  አንብቡት ሊነኩን ከጽሁፉ መጨረሻ ላይ ያገኙታል ።
Ø  የጸረ አማራ የጥላቻ መርዘኛ መርፌ የተወጋ
"መከረኛው አማራ"  ነው ያልክ ዳኒ እውነትክን ነው ቆይ እኔ ግን የኢሐዲግ ደጋፊ ለመሆን መገለጫው አማራን መጥላት ሆነ እንዴ ?  ዳኒ የምን ሐገር ልጂ ብቻ ሳየሆነ ከነሰፈሩ ስለማቅ እኔ ስለዚ ስታነሳ ምንም ብትል አይደንቀኝም ። እሚገርምህ ጣና ደሴቶች ላይ መጽሀፍትን ሲያነብ ያደገ ሰው ነው የጣናንና የዓባይን ውሐ ተራጭቶ አድጎ ማንም መሬቱን ወገኑን አይጠላም ወንድሜ መርፌውም ቢሆን አቅሙን ያጣል መርዘኝነቱ ቀርቶ መድሐኒት ይሆናል ዝም ያለ ሕዝብ ሁሉ ዝም ያለው ስለደገፈ ነው ብለህ ነው ? …. አናጋሪወች ሆይ አታናግሩን እባካቹ እንደ  ኢትዮጵያ ብቻ እንድናስብ ተውን ። 
Ø  ተናክሶ ዞር ይላል እንጅ ለመወያየት የሐሳብ ፍጭት ለማድረግ ፈጽሞ አይፈልግም፡፡
እውነት እንነጋገር ከተባለ ዳኒ ለ አቶ ኤርምያ መልስ መስጠቱ በራሱ አስገራሚ ነው ማንም በተንጫጫ ቁጥር ከተንጫጫህማ አንተም የልጂ ጨዋታ አርገህዋል ማት ነው። እዚ በላይ እንዴት ይነጋገር ነው ወይስ እንደ ኤርምያሳቹ ሁለተኛ የመጨረሻ ምላሽ ብሎ የናንተ ብሎጎች ዳግም አድማቂ እንዲሆን ፈልጋቹ ነው ? ያን ባለማድረጉ ቅር ተሰኛቸሁ ? ከዚ በላይ ምን ያርግ  እንዲውም ጠበቅ አርጎ እስኪበቃው ጭኖታል ነው ቀለል ያለው መስሎህ ነው ? ወይስ ቀድመህ መልስልኝ አይነት ማመልከቻ እያስገባህ ነው ? ምን ቁም ነገር ያለው ትችት አቀረብክና ይመለስልህ ? ለናንተማ እኮ የልጅ ልጆቹ በቂ ነን ። ልጅ የወለደ እኮ መናገርን ለልጆቹ ትቶ እሱ ስራውን እሚሰራው ልጆቹ ላይ ነው ።
Ø  የጻፏቸውን የወያኔን ግፍና ወንጀል የሚያጋልጡ መጻሕፍቶቻቸውንም በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነት እንዳያገኙ እንደ ምንም ብሎ ይጠጋና የጻፉት ሐሰትና የፈጠራ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ ኤርሚያስ ለገሰ፣ ተስፋየ ገብረአብ የመሳሰሉት፡፡
አይዞህ ሌላ ሌላ አትግባ ለምን ኤርምያስን ነካህብን ብለህ ብትነሳ እኮ ማንም አይቃወምሕም ። አሁን ስለ ኤርምያስ ለገሰ ስትጽፍ ትንሽ እንኳን አታፍርም ክ 8 ዓመት በፊት በተፃፈ ጽሁፍ ላይ እንዲ የወረደ ተቃውሞ ስለሚያቀርብ ሰው ? ለሁሉ ሲመልስ እሚውል እኮ እሱ ቦዘኔ ነው እነፌስቡክ ሁሉ የጸሐፊነት ካባ ለደረቡለት ጸሃፊ ነኝ ባይ መልስ ሰጠህማ እንዴት ትጭለዋለህ ?
ተአማኒነት እንዳይኖረው የሆነው ያእሱ አ/ቶ ኤርምያስ ነው ያለምክንያት ያለመረጃ ከጻፈ እሱ ተላንት ምን እነደጻፈ እርግጠኛ መሆን ይቻላል ይሐየኔ ነው "አውላላው ሜዳ ላይ የተኛውን በሬ ነካክተው ነካክተው አደረጉት አውሬ ማለት " ሳይሉአችሁ ነክታቹ ክብራቹን አጣቹ።
Ø  መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ
 እኔ የሰሞኑ ጸሃፊወች እጅግ እየገረማችሁኝ ያለው በሰዓቱ ለማውራት አድፍጣችሁ ቆይታችሁ አሁን ቱቱቱ … ማብዛታቹ ነው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ዳኒ በሰዓቱ በበቂ እና ጸሐፊውን እጂግ ባከበረ መልኩ ትችቱን አቅርቧል ቆንጽሎ ላልለከው ርዕሱ ሁሉን ይገልጣልና ርዕሱ ካላማረ ስለ ርዕሱ ሳታወራ እንዴት ስለ ውስጡ ታወራለሕ?  ወንድሜ ሆይ አሁንም ዳኒ ልክ ነው ቢከሽፍ ነገ እንጂ ታሪክ አይከሽፍም የሆነ ነገር እንዴት ተመልሶ ሊከሽፍ ይችላል ? ማነጻጸሪያህ ደሞ እጂግ  ይገርማል “እኔ እንዲያው ታሪክን ኤዲት ማድረግ ቢቻል ይሄ ዘመነ መሳፍንት የሚባለውን መጥፎ የታሪካችን ክፍል ቆርጨ ከታሪካችን አወጣው ነበር” ይህ አባባል ከታሪክ መክሸፍ ጋር ምን አገናኘው ነው ክሽፈትና ምኞት አንድ ናቸው ባንተ ቤት ? እውነት አንተ ትላንት ይሕ ባይሆን ብለህ ተመኝተህ አታቅም ? ያኔ ትላንትን እያከሸፍክ ነው እንዴ ?
Ø  "የዳንኤልን ጽሑፎች የሚያነቡ ሰዎች እንደሚሉት እስከ ዛሬ ድረስ ለአንድም ጊዜ እንኳን ቢሆን ጸሐፊ ነኝ እንደማለቱ በወያኔ ከሰብአዊ መብት ገፈፋ እስከ የዘር ማጥፋት ከሙስና በዜጎች ላይ እስከሚፈጸሙ ኢሰብአዊ ጥቃቶች ከአሥተዳደር በደሎች እስከ ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት መነፈግና ያለ ጣልቃ ገብነት እምነትን በነጻ የማራመድ መብትን እስከማጣት በታመሰች ሀገር ውስጥ ሆኖ እንደጸሐፊ አይደለም እንደዜጋ እንኳን በእነዚህ ነገሮች ላይ አንድም ነገር ተናግሮ ተንፍሶ አያውቅም፡፡ እዚህ ላይ ግን ጌቶቹ ማለት ወያኔ ስሕተት ሠርቷል እንዳይጠረጠርበት ለማድረግ ለማስመሰል እንኳን በአንዳንድ ነገሮች ላይ እየተቃወመ እንዲጽፍ ለምን ማድረግ እንዳልፈለገ ይገርመኛል፡፡"   ይህን ሳነብ አሁን ገባኝ እና አሳዘንከኝ ምንም ስለማታቀው ሰው ነው ለካ ወንድሜ እምታወራው ዝም ባለ አፍ   . . .    ሲባል አልሰማህም  መጀመርያ አንተ እንደ ጸሐፊ  "የዳንኤልን ጽሑፎች የሚያነቡ ሰዎች እንደሚሉት" እንደሚሉት እያልክ ሒስ ትሰጣለህ እስኪ እንዲ ልጽፍ ስትነሳ እንኳን ቢያንስ ጽሁፎቹን አንብበህ አትጽፍም ነው ወይስ ስትነሳም በጭፍን ተነስተህ ለመወረፍ የተነሳሕ ነህ ???  ያልገባህ ምን መሰለህ ዳኒ ጽሁፎችን ሲጽፍ እንዳንተ ወይም እንደጭፍን ተቃዋሚወች ሰውን በሚያውክና እንዲነበብልን ብለን እንደምንጽፋቸው አስበርጋጊ ርዕሶች አይደለም እሱ ስለ ዱር አራዊት እያወራ ይነግርሐል እሱ  ስለ አይጦች እየተናገረ ብሶትክን ይተነፍስልሀል እሱ ተነስ ጩህ ሩጥ  ተዋጋ ሳይሆን ከስሜታዊነት የወጣ ጽሁፍን ይጽፋል እስኪ ወንድሜ የእውነት ተቆርቋሪ ከሆንክ ከቻልክ አራቱን የወግ መጽሃፍቱን ገዝተክ እስከ ኃሙስ ከቆየህ ደግሞ አምስተኛው ይወጣል ካልቻልክ ብሎጉን አገላብጠህ አንብበው አንተ እራስሕ ይቅርታ ትጠይቃለህ ስለስሕተትሕ ።
Ø  "ይመስለኛል እኔ የዳንኤልን ጽሑፎች ስላላነበብኩ እንጅ እርግጠኛ ነኝ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ባሉ ጽሑፎቹና ቃለ መጠይቆቹ ሌሎች ተመሳሳይ ነውረኛና መሠሪ ድርጊቶቹን ሊገልጡ የሚችሉ ጽሑፎችም ሆኑ ንግግሮች ይኖራሉ፡፡"
ሌላስ የሚመስልሕ የለም የይመስለኛል ተራኪው ወንድማችን ? እንዴት ነው ስታየን አሻንጉሊት መጫወቻ እንመስላለን እንዴ በይመስለኛል ልታወራን እምትሞክረው ? በይመስለኛል በይመስለኛል እማ ሳስበው ሳስበው አ/ቶ ኤርምያስ የመጨረሻ ብሎ ከጻፈ በኋላ ቆቸውና ጻፍልኝ ብሎህ ነው አይደል  ይመስለኛል አይደል ምን ችግር አለ ቢመስለኝ መምሰል አይከለከል ።
Ø  "እኔ ዳንኤል መመረዙን ለመጀመሪያ ጊዜ የተረዳሁት የላይፍ መጽሔት በቅጽ 7 ቁጥር 102 መጋቢት 2005ዓ.ም. ከእሱ ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ባነበብኩ ጊዜ ነበር፡፡ ይመስለኛል እኔ የዳንኤልን ጽሑፎች ስላላነበብኩ እንጅ እርግጠኛ ነኝ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ባሉ ጽሑፎቹና ቃለ መጠይቆቹ ሌሎች ተመሳሳይ ነውረኛና መሠሪ ድርጊቶቹን ሊገልጡ የሚችሉ ጽሑፎችም ሆኑ ንግግሮች ይኖራሉ፡፡ በጠቀስኩት ወቅት ከላይፍ መጽሔት ጋር አድርጎት የነበረው ቃለ መጠይቅ ግን የልጁን ማንነት (የልጁን አልኩኝ? የስንት ጊዜ ታላቄን) ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር፡፡ እንዳነበብኩት ሰው መስሎ አልታይህ ነበር ያለኝ፡፡ ከሱ ያልጠበኩት ቆሻሻና እርኩስ አረማዊ ማንነቱ ኅሊናየን እጅግ እረበሸው፡፡ ፎቶዎቹን ሳይ ዲያብሎስን ያየሁ ያህል ይቀፈኝ ጀመር፡፡ ግን ለምን እያልኩ እራሴን ደጋግሜ ጠየኩ በወቅቱ ጥቅም በልጦበት ተራ ጥቅም ፍለጋ ወይም ደግሞ ሚስቱ ትግሬ ስለሆነች ሚስቱን ለማስደሰት መስሎኝ ነበር፡፡ ነገሩ እየጠራ ሲመጣ ግን ከተራ ጥቅም ፍለጋና ሚስቱን ከማስደሰትም በላይ የከበደ ሆኖ አገኘሁት፡፡በዚያ መጽሔት ላይ ዳንኤል በቃለ መጠይቁ የተናገራቸው ነገሮችንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚቀጥለው ጊዜ እመለስበታለሁ"
ለቁም ነገር እንደምታወራ እሚያሳብቅብህ እሄን ያክል ጽፈህ በሚቀጥለው ጊዜ ብለሕ ማቆምህ ነው ነው ተከታታይ ፊልም ጀመርክብን ቁጭ አርገህን ?  እምትናገረው ከሌለህ እኮ ዝም በማለት ቅጣት የለብሕም ።
Ø  “ነቢዩ መሐመድ” እያለ ለምን ይጽፋል ነብይነቱን ይቀበላል ማለት ነው
በግሌ ዳኒ ዲያቆን ይሁን እንጂ ጽሁፎችን እሚጽፈውም እንዲያነቡ እሚፈልገውም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው ከሁላችንም መሀል ኢትዮጵያዊነት አለ ስለ ኢትዮጵያዊነት ስታወራ የአንዱን ሃይማት እየነካሕ ሳይሆን የሱን አክብረህ ልትጽፍ ይገባል ያኔ ስለ ኢትዮጵያዊነት ማውራት ትችላለህ አንድን ሰው አንተ እኮ የተሳሳትክ ነህ ብለህ ስለሌላ ቁም ነገር ብታወራው እንዴት ትቀበለዋለህ ?
በሐገራችንም እኮ ችግር የሆነብን እኮ ይህ ነው እምንጀምረው ሙሉውን ተቃውመን ነው ። ሙሉውን ተቃውመህ ጀምረህ ምን በጎ ነገር ሰው እንዲቀበልህ አንተስ መልካም ነገር እንዲታይህ ትጠብቃለህ ወንድሜ ?
Ø  "ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሊያርሙት የሚፈልጉት ሰው ዓይነት አለውና ለዚያ የማይበቃ ሆኖባቸው ንቀው ዝም ሲሉት ጊዜ ዐዋቂ ነው የተባለ መስሎት እራሱን አንቱ አለ በትዕቢት ወጠረ፡፡"
እቺ ዓረፍተ ነገር እንዴት ሊቃውንቱ ዝም አሉ እንዳትባል ያነሳሃት ናት ? እነሱ እኮ አይደለም ስለዳንኤል ስለነ በጋሻውም ተሰብስበዋል ወንድሜ ?  አንተ እኮ ትልቅን ትንሽ ስላልከው ትንሽ አይሆንም ።
Ø  "አንድ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይማር ምሥጢር ሳይጠነቅቅ ባለ ንስር ዐይን ነኝ ብሎ ቁጭ አለ፡፡ አይገርምም?"
እስኪ አልተማረም ብለን እናስብ እና ባለመማሩ አይደል እንዲ ድንቅ አስተማሪ የሆነው እንዲ እንደ ንስር አይን ሆኖ ያላየነውን የናቅነውን አጉልቶ እሚያሳየን አሰይ እንኳን አልተማረልን አለመማር እንዲ ከሆን ሁሉም ባይማር እንዴት ነበር ። ተማሩ ብለን ያወራንላቸው አንዳንዶቹ የትስ ነው ያሉት ? የንስር አይን ነኝ አለ ማለትክን ሳነብ ይልቁንስ ከላይ እንኳ ቅድም አንብቤው አላቀውም ያልከውን ብሎጉን ማንበብክን አሳበቀብህ አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል ማለት ይህ ነው ።
Ø  የሚገርመው እንዲህ ዓይነት ሰው ሆኖ አሁንም እሰብካለሁ እያለ በየጉባኤው መቆሙ ነው፡፡
እሱ ምን ይገርምሀል "ሙሐዘ ጥበባት " መባሉን ብትሰማ እንዴት ልትሆን ነው ?



እንግዲሕስ ምን እንላለን ጸሃፊያችን እንዲ ጽፎ ነው ትንሽም ግራ ያጋባን እኔ ማኔ-ቴቄል-ፋሬስ ብያለሁ ። ሰዓልያን ሆይ እናንተም ወደስዕላችሁ ሙኃዘ ጥበባትም ወደጥበቡ
ዳኒም በቃሉ ሳይሆን በተግባር ይህን መልዕክት አስተላልፎልሀል "ስራ ላይ ነን ለወሬ ጊዜ የለንም ።" ሰሞኑን ሐሙስ 17/7/07 "እኛ የመጨረሻወቹ እና ሌሎች"  አምስተኛው የወግ መጽሐፍ ገበያ ላይ ይወጣል ።

                    ይቆየን 

0 አስተያቶች:

Post a Comment

Facebook Twitter Addthis Google+