ቀዳሚ ገጽ » » የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ

የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ

Written By bahir dar city foot ball club on Wednesday, March 18, 2015 | 9:06 AM

ትላን ባይኖር ዛሬ የለም ለዛሬ ምቾት የትላንት ጥረት ለዛሬ ሰላም መሆን የትላንት መስዋዕትነት ለዛሬ ጥጋብ የትላንት መራብ …. ላጠቃላይ የዛሬ ማንነት የትላንቱ አሻራ እጅግ ከፍተኛ ነው
·         ለዛሬ አንድ ኢትዮጵያ መኖር …..  ከአጼ ቴወድሮስ ጀምሮ ያሉት ነገስታት አሻራ
·         ለዛሬ የባቡር ፕሮጀክት…..ከ 100 ዓመት በፊት አጼ ምንሊክ ያስገቡት ባቡር
·         ለዛሬ እንችላን የሚል በራስ መተማመን …ጣልያንን ለማባረር የተሰው ሰማዕታት
·         ለዛሬ የካቲት 11 መከበር…… ትላንት ለትግሉ መስዋዕት የሆኑ ሰማዕታት
በአጠቃላይ ለዛሬ ትላንት ዋናው አሻራ ነው


እናት አገራችን ኢትዮጵያ ከብዙ ሺህ ዓመታት ጀምሮ ከቅርብ ጎረቤቶችና ከሩቅ ጎረቤቶች ትነኮሳ ሲካሄድባት በቆራጥ ሌጆቹዋ መስዋዕትነት ጠሊቶቹዋን ድሌ እያረገች እነሆ እስከዛሬ ነጻነቱዋን አስከብራ ኖራለች፡፡
የዛሬ 79 ዓመት 1928.. ፋሽስት ኢጣልያ ከአርባ ዓመት በፊት በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ አመራር  የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል ዘመናዊ የጦር መሣሪዎችን ታጥቃ በአውሮፕላን ፤በታንክና በመርዝ ጢስ በመጠቀም  ተንደርድራ  አዲስ አበባን  ተቆጣጠረች፡፡ ይህ ሲሆን የኢትዮጵያ ልጆች በየአካባቢያቸው የጎበዝ አለቃ መርጠው ጠላት ሰላም ተነስቶ እንየተቅበዘበዘ ለአምስት አመት ብቻ በየከተሞች በየካምፑ ተወስኖ እንዱቆይ አድርገውታሌ፡፡
በአዲስ አበባ የፋሽስት ሀይል በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል አይተው  ህሊናቸው  እጀግ  የቆረቆራቸው  ሞገስ አስገዶምና  አብርሃም ደቦጭ የተባሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን  የሙሶሉኒ  ቀኝ እጅ የነበረውና  ኢትዮጵያን እንዲያስተዲድር  የተላከው  ሩዶሌፎ  ግራዚያኒን  ለመግደል የወረወሩበት ቦምብ ሳይገድለው ቀረ፡፡ ግን ክፉኛ ቆሰለ፡፡ ሆኖም በድርጊቱ እጅግ የተበሳጨው ግራዚያኒ ጥቁር ሸሚዝ ለባሽ የተባለትን የፋሽስት ጦር ጨካኝ ቡድን በአዲስ አበባ ሕዝብ ሊይ አዘመተ፡፡ በዚች ከዛሬዋ ዕለት 1929 .. እስከ የካቲት 14 ቀን በሦስተ ቀናት ብቻ 30000 ( ሠሊሳ ሺህ)የሚሆን ህዝብ ተጨፈጨፈ፡፡ ጭፍጨፋውም በርሸና በስቅሊትና በእሳት በመለብለብ  ነበር
አቡነ ጱጥሮስ እና አቡነ ሚካኤሌ ሕዝብ ለፋሽስት ሀይሌ እንዲይገዛ ያወገዙት አባቶች ያለርህራሄ  ተረሽነዋሌ፡፡ በደብረ ሉባኖስ ገዳም ይገኙ የነበሩ 300( ሦስት መቶ) መነኮሳት በግፍ ተጨፍጭፈዋል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦች በአዲስ አበባና ከዚያም ውጭ በሚገኙ እሥር ቤቶች ተወርውረው እንዲማቅቁ ተደርገዋል፡፡ ይህን ሁሉ   በደል  የፈጸመው  ግራዚያኒ ... 1948 .. በዓለም   ጦር  ፍርድ ቤት ቀርቦ በኢትዮጵያዊያንና በሉቢያዊያን የፈጸመው ግፍ በማስረጃ በመረጋገጡ  19 ዓመታት በጽኑ እሥራት እንዱቀጣ  ተፈርዶበት ወደ ወይሂኒ ቤት ተወርውሮ ከሁለት ዓመት እስራት በሁዋላ ተፈቶ በድዛውን አጥፍቶ ኖሩዋል፡፡
 ግራዚያኒ ያንሁሉ  ጭፍጨፋ በአካሄደ 76 ዓመት ... ነሐሴ 11 ቀን 2012 በሮም አጠገብ በምትገኝ መንለር የኢጣሊያ መንግስት ተወካይና የቫቲካን ተጠሪ ባለበት በትሌቅ ስነ ሥርዓት የተሠራለት ሃውልት ተመርቁዋል፡፡ የንጹሀንን  ደም በከንቱ  ያፈሰሰ  አውሬ ጀግና ተብሎ መከበሩ የሰው ልጅ ደህንነት የሚቆረቆርን ሁሉ አስገርሙዋል፡፡ ይህ ድርጊት እንዱቀለበስ  በዓለም ዙሪያ  እንቅስቃሴ  እየተረገ ነው፡፡
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ድርጊቱ አስቆጥቶት ሀውልቱ እንዲፈርስ በመጠየቅ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶበታል፡፡
የፋሽስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶልኒ በኢትዮጵያና በጣሉያን ሕዝቦች ሊይ ላደረሰው ግፍ ወደር የሌለው እንደነበር በሕይወት ያለና የታሪክ ተመራማሪዎች በታሪክ መዛግብት የሰጡት የምስክርነት ቃል አረጋግጡዋል፡፡
በጣልያን አገር በመጨረሻዋ ሰዓት ሞሶሉኒ በጣልያን አርበኞች እጅ እንዲይወድቅ ሲቅበዘበዝ ተይዞ በጥይት ከተደበደበ በሁዋላ  ሬሳው ወደ ሚላን ተወስዶ ተዘቅዝቆ መሰቀል ምን ያህል ህዝብ እንደጠላው ያሳያል፡፡ ይህን ግፈኛ ዛሬ ሞሶሉኒ በሰው ላይ ጥይት ተኩሶ አያውቅም ፤መልካም አስተዳዳሪ እንደነበር የሚመሰክሩ የጣልያን ፖለቲከኞች ቀና ቀና ማለት ጀምረዋል፡፡
ይህ አባባል በንጹሃን ደም ማላገጥ ይሆናል፡፡ ይህን አስተሳሰብ የሚያራምደት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ መልካም ነው እውነትን መሸሸት እንዴት ይቻላ እንዴትስ ይሆናል
                    ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቹዋ መስዋዕትነት ለዘላለም ታፍራ ትኖራለች !



v  የካቲት 12 ቀን 2005 ዓ. ም. የሰማዕታት ቀን ሲከበር የጥንታዊት ኢትዮጵያ

ጀግኖች አርበኞች ማህበር ተወካይ የተረገ ንግግር

0 አስተያቶች:

Post a Comment

Facebook Twitter Addthis Google+