ቁማር እሚለውን ቃል
መጠቀም ቢከብደኝም ስራውን ሳስብ ደግሞ እምገልጽበት ቃል አጣሁ ስለዚህ አልኩት ። አንዴ በቁማር ሱስ ውስጥ የገባ ሰው ሱስ ደረጃ
በቀላሉ ይደርስና ያንን ሱሱን ለመተው እጅግ ከብዶት ሁሌም በዛ ልማድ ውስጥ እናገኘዋልን ።
በሱስ ውስጥ የተዘፈቀ ቁማርተኛ በነገሮች
ላይ ለመቆመር ሆነ ሁሉን ነገር ለማስያዝ ግድ የለውም ። ለሱሰኛ ቤት ቤተሰብ ሕዝብ መሬት ቦታ ማንነት ምንም ዓይነት ቦታ የላቸውም
ብቻ እሱ በቁማሩ ውስጥ ቅድሚያ ተጠቃሚ ይሁን ከራስ በላይ ነፋስ
እሚለው ብሒል እሚሰራው ለእንደነዚህ አይነቱ ነው ።
እማወራው ከሰሞኑ በአማራ
ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር ስለተከናወነው ነገር ነው ። የሰው ሕይወት ባለፈበት ሁኔታ ውስጥ ለእኔ ትልቁ ቁማርተኛ ሆኖ ሐላፊነቱንም
መውሰድ ዓለበት ብየ እማምነው እንደ ደሕና ማዕከል መቀመጫውን መሃል ከተማ አርጎ ቁማርተኞችን የሰበሰበው ቤተክሕነት ነው ። መጀመርያ
ለቤተክርስትያን ሳይሆን ለግል ጥቅማቸው በተሰባሰቡ ግልጽ የሆነና
አይን ያወጣ ጥፋትን ዝም ብለው ሲያሳልፉ ዝም ያልናቸው ከታች እስከላይ መረባቸውን የዘረጉ ለቤተክርስትያን የእፉኝት ልጅ ሆነውባት
ሊያጠፏት የተቀመጡ ማንም ነቅናቂ የሌላቸው እና ስለ ምንም ነገር ግድ የሌላቸው ስብስቦች ናቸው ።
በዛ ቢሮ ውስጥ እኮ ስንት ስለ ቤተክረስትያን የሚገዳቸው ሰወች ስለ ቤተክርስትያናቸው እያለቀሱ
ተገፍትረው ወጠዋል ? ስንቶችስ ስለ እውነት ስለጠየቁ የፖሊስ ሀይል ተደውሎ ወንበዴወች እየበጠበጡን ነው አስወጡልን ተብለው ተባርዋል
? ለነ እሱ እኮ ቤተክርስትያንን እኮ የምዕመናን ብቻ ነው የምትመስላቸው ስንት ያልጠነከሩ ወንድሞቻችን እኮ እች ናት እንዴ ቤተክርስትያን?
ብለው ከአንድነታችን ትተው ሄደዋል ።
የሆነ ቦታን አስባችሁ
ዝም ብሎ እሚያንገሸግሻችሁ ነገር የለም እኔም የገፈጡ ቀማሽ ስለነበርኩ ስለዚህ ቤት ሳስብ እሚሰማኝ ይህ ነው። በእኔ እይታ ስለ አሁኑ ሰላማዊ ሰልፍ የቤተክህነቱ ጥፋት ያልኩትን ላስቀምጥ።
Ø
ለሕዝቡ ግልጽ የሆነ መረጃን አለመስጠት ።
ቦታው ተፈለገው ለመንገድ ነው ወይስ ለሌላ
ልማታዊ ስራ ? ለባለሃብቶች ወይስ ለሐገር ጥቅም እሚውል ቦታ ?
ከመስቀል አደባባይ እሚፈለገው ምን ያክል
ቦታ ነው ? ሁሉም ወይስ እነሱ እንደሚሉት 2 ሜትር ወይስ ሰው እንዳሰበው 7 ሜትር ?
Ø
መንግስት እንደሚለው ተስማመተው ፈርመው ከሆነ።
መስቀል አደባባይ የቤተክርስትያኗ
ንብረት እንደመሆኑ መንግስት ቀጥታ እሚነጋገርው ለዛ ቦታ ኃላፊነቱን ከሚወስደው የቤተክርስትያን አካል ጋር ነው እሱም የባህር ዳር
ሐገረ ስብከት ነው አሁን መንግስት አወያይቻለው እናም ተስማምተናል ብሏል እንደዛ ከሆነ በምን ስምምነት
እንደተስማሙ ሀገረ ስብከቱ ለሰው ማሳወቁ የግድ ነበር በጨረሰው ነገር ላይ ሰው ሲፋጂ ቁሞ መመልከት ምን ማለት ነው ።
Ø
ስለቤተክርስትያን ሰው አልፎ ሰው እየታሰረ ዝምታው ምንድን ነው
?
ምክንያቱ ምንም ይሁን ሰው ስለቤተክርስትያን
ነው የወጣው ሰውም አልፏል አለፈ ግን ቤተክርስትያንም ስለ ልጆቿ
እኮ ሊገዳት ይገባል ምንም ቢቀር የክርታ እኮ ያስፈልጋል ነፍስ ሰላለፈበት ነገርም እኮ ትክክለኛ ምክንያት ሊቀመጥ ይገባል ልጆች
ለምን እምትል እናት እኮ ልጆች ይናፍቃሉ። ለቆሰሉት ልጆቿ
ካሳ እምትሆናቸው ቤተክርስትያን ሊጆች ይፈለጋሉ።
በእኔ አመለካከት ቤተክርስትያናችን
ልማትን አትቃወምም ልትቃወምም አይገባትም ፍትሐዊ እስከሆን ድረስ እኔ በውስጤ ያሉ ጥያቄወች
፩ ቦታው መንገድ ከሆነ እና ሁለት ሜትር ብቻ ከሆን እሚገባው
ለምን ወደ መስቀል አደባባይ ብቻ እንዲሆን ተመረጠ ?
ያለ ምክንያት ጥያቄውን
አላነሳሁም ከአዝዋ እስከ ጊወን ሆቴል በ 50 ሚልየን ብር ሊሰራ የታሰበው የ አንድ ኪሎሜትር መንግድ ለሁላችንም ጠቃሚ መሆኑ ጥርጥር የለውም ግን በምን አግባብነት ነው ሁለት ሜትሩ ውደ ቀኝ በኩል እንዲሆን
የተፈለገው ? ወደ ግራ መስመር ከሆን የሙስሊሞችን መስጂድ ይነካል
ወደ ቀኝ የ ኦርቶዶክስን መስቀል አደባባይ ?
፪ የአጥሩ ወጭ የታሰበው እንዴት ነው ?
ሁለት ሜትርም አንድ ሜትርም ገባ አጥሩ መፍረሱ እማይቀር ነው ስለዚህ ከፈረሰ
አጥሩ በማን ወጪ እንዲሰራ ታሰበ ?
፫ ሠላምን እና መስማማትን ሲባልፕላኑ ቢለወጥስ ?
ለሁሉም አካል መፍትሔው
ሠላም ብቻ ነው ከፓፒረስ ጊዮርጊስ ያለውን መንገድ ታሳቢ በማድረግ ከአሁኑ መንገድ ላይ የታሰበውን የ ብስክሌት ምስመር ተቀናሽ
አድርጎ ወደ አደባባዩ መግባቱ ቢቀር ትልቅ የሠላም አማራጭ ይመስላል።
ለማጠቃለል ያክል አሁንም
ነገሮችን በሠላማዊ መንገድ ከመፍታት የተሻለ አማራጭ የለም ያን ለማድረግ ደግሞ መልካም የሆኑ አባቶች እና ምዕመኑ እሚተማመንበት
ሐገረ ስብከት ያስፈልጋል ከጠቅላይ ቤተክሕነትም ቢሆን ሰው ለመፍትሔ መሔድ አለበት ።
ስልቤተክርስትያን ነፍሳቸውን የሰው የተጎዱ ሰወችም ኃላፊነቱን እሚወስድ አካል ያስፈልጋል ።
ቁማርተኞችም ከነ ቁማራቸው ቤቱን ሊለቁ ያስፈለጋል ።
ይህ ቁማር ከቀጠለ ግን
ቤተክርስትያኗን ያለ ምዕመን እንዳያስቀራት አሁንም ያሰጋል ።
ቁጭ ብለው አሱ ነው እሱን እሰሩት ማለት ስልጣን መስሏቸው ልጆቿን እሚያስበሉም በምድር ሳይሆን
በሰማይ የደም ዋጋ አለባቸው ። ወንጌልን ማዳረስ የሰማይ ያክል እርቆባቸው መድረክ ላይ እንኳ
ወጠው ስለ ሠማያዊው ሳይሆን ምድራዊው መንግስት እሚሰብኩ እነሱ ዛሬ ቢዘሉም ቀኑ ይደርስና ስለ ሁሉም ይጠየቃሉ።
በቤቱ ያላችሁ ቅን አባቶች
ሆይ በረከታቹ ይድረሰን ሰለወንጌሉ የደክማቹ እናንተ እድሚያቹ ይርዘምልን
።
ገዳዮች ሆይ የጥፋት ዋጋቹ በሰማይ ነውና ደስ ይበላቹ እንደፈለጋቹ ስትሆኑ
አምላክ ዝም ስላላቹ ትክክል የሆናቹ መስሏቹ
ደስ አይበላቹ ለሁሉም ጊዜ አለው ።
ወንድሞች እና እህቶች
ወይ በጥርሱ ፈገግ ብሎ ችግር የለም እያለ በጎን የሚሸጡን ቁማርተኞች እስካሉ ድረስ ድካማችን መሞታችን ከንቱ እንዳይሆን አስተዋይ
እንሁን ።
0 አስተያቶች:
Post a Comment