ቀዳሚ ገጽ » » የባህር ዳር ሐገረ ስብከት ያስገነባው መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመረቀ

የባህር ዳር ሐገረ ስብከት ያስገነባው መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመረቀ

Written By bahir dar city foot ball club on Friday, April 17, 2015 | 10:51 PM

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የባህር ዳር ሐገረ ስብከት ያስገነባው መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመረቀ 
ኮሌጁ በባህር ዳር ከተማ ከባህርዳር ዩንቨርሲቲየ ጎን ከፈለገ ግዮን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ላይ 21000 ሜትር ስኩዌር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ለግንባታ 3.8 ሚልዮን ብር ወጪ ተደርጓል
ሙሉ ወጪውም በሐገረ ስብከቱ ተሸፍል ግንባታውም ያለግንባታ ያለፉ ጊዚያትን ሳይጨምር 15 ወራትን ፈጅ
የግንባታው ቦታ የተመረጠበትን ምክንያት እንዲህ ሲሉ የሐገረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ አስረድተዋል
1.   የቦታው መልክዐ ምድር ጥሩ መንፈስን እሚፈጥር መሆኑ የአባይ ወንዝ ለሁለት ተከፍሎ ደሴት እሚሰራበት ቦታ ላይ መገንባቱ
2.   ከ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጎን መቀመጡ ለተለያዩ እገዛወች አመቺ ይሆናል
3.   ከከተማው ራቅ ማለቱ ለጥናት አመቺ ቦታ ስለሆን በማለት
ግንባታው ለጊዜው አራት ብሎኮችን የያዘ ሲሆን
·         የመጀመርያው ብሎክ የተማሪወች ማደሪያን የያዘ ሲሆን እስከ 8 ሰው  ማስተናገድ እሚችሉ የተለያዩ 15 ክፍሎችን ይ
·         ሁለተኛው ብሎክ 3 የመማርያ ክፍሎችን
·         ሶስተኛው ብሎክ  መመገቢያና የማብሰያ ክፍል
·         አራተኛው የ መምህራንና አስተዳደር ቢሮ ሽንትቤትና ሻወርን ካቶ ተገንብ
ኮሌጁ ሚያዝያ 8 ኃሙስ  
Ø  ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ
Ø  አቡነ ጴጥሮስ
Ø  አቡነ ማርቆስ
Ø  አቡነ ጎርጎርዮስ
Ø  አቡነ ሔኖክ
Ø  አ/ቶ ሰማ የክልሉ መንግስት  ልዩ አማካሪ
Ø  የ አዲስአበባ ከተማ ደብር ጨምሮ የተለያዩ ደብር አስተዳዳሪወች
Ø  ሊቃነ ጳጳሳቱን ያፈሩ ታላላቅ ሊቃውንት መምህራን ና ተጋባ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል

በምረቃ መርሐግብሩም ቅኔና የመሳሰሉ መርሐግብራት ተከውነዋል

0 አስተያቶች:

Post a Comment

Facebook Twitter Addthis Google+