ቀዳሚ ገጽ » » “በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ይሰደባል ።” ሮሜ 2፥24

“በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ይሰደባል ።” ሮሜ 2፥24

Written By bahir dar city foot ball club on Saturday, August 15, 2015 | 2:27 AM




ዛሬ ለዚህ ጥቅስ መነሻ የሆነኝ እና ከብዙ ጊዜ በኋላ ልጽፍ ያስነሳኝ በጠዋት እንደተነሳሁ ያነበብኩት የመምህር ዘመድኩን “ሰበር ዜና ” የሚል እራሱን “ትክክል ነኝ” ብሎ ከሚያስብ መምህር የሚጠበቅ ጽሁፍ ማንበብ ነው ። አንድ እንድንረዳው እሚያሰፈልግ ነገር አንድን ጽሁፍ በራሱ መቃወም ማለት ከዛ ጽሁፍ በተቃራኒው ያሉ ሰወችን ወይም ቡድንን መደገፍ ማለት አይደለም ። መምህር ዘመድኩን “አርማጌዶን ” በሚል ባወጣው ሲዲው መረጃወችን ካደረሰ በኋላ አዲስ ማንንት ይዞ ብቅ ያለ መምሕር ነው ። ብዙ ጊዜ አንድን ቡድን በመቃወም ላይ ነው እምናየው ። ተቃውሞውን ሳይሆን የተቃውሞውን መገለጫ  እቃወማለሁ  እሚቃወመው ግለሰብን ከሆነ ጠቡ ከግለሰቡ እንጂ ከሚያራምደው ሃይማኖት አይደለም አካሄዱን(የሃይማኖት ሕጸጽን) እሚቃወም ከሆነ ግን መጻፍ ያለበት ስለምንፍቅናው(ስለ አስተምህሮው ስሕተት)  መሆን አለበት ።
“ሰበር ዜና” ብሎ ባወጣው ጽሁፉ ላይ እምናየው ግን ፈጽሞ የግለሰብ ጥላቻ የሆነን ጽሁፍ ነው ። ሰበር ዜናውም የቡድኖቹ ለሁለት መከፈል እንደ ደስታ ዜና አድርጎ እያስደመጠን ነው ። ቀጥታ እሚመለከተው ግለሰቦችን ነው ይህ ደግሞ መንገድን ሳይሆን ጥላቻን መስበክ ነው ። ጥላቻን ደግሞ ማንም አስተምሩ ብሎ አላከም   “ ወደ ጠፉት በጎች ኂዱ  ሄዳችሁም መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ።” ማቴ 10፥7 እንጂ ።

 ነገር ግን እኔ በራሴ ግንዛቤ መጠን የመምሕሩ አጻጻፍ ለማንኛውም ወገን እሚጠቅም አይደለም ይህንን ያልኩበትን ምክንያት።
1፦ በግለሰቦች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ መጻፉ።
“ፓስተሩ እስካሁን ለማመሰል እንደሌሎቹ ያላገባና  የመበለቶች ወዳጅ ሆኖ በጽኑ ደዌ የተያዘ ሰው ነው ።” ይለናል መምህሩ።    አንድ መጽሐፍ ምርቃት ላይ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ እንዲ ያሉት ቃል አስታወሰኝ “ አቃቢ ሃይማኖት የሆኑ ጽሁፈች ሲጻፉ ትኩረታቸው ሊሆን እሚገባው  በአስተምሕሮው(ምንፍቅናው) ላይ እንጂ በግለሰቡ ላይ ሊሆን አይገባም ።” ምዕመኑ ማወቅ ያለበት ይህ መንገድ ትክክል አይደለም እንጂ እሱ እኮ እንዲህ እንዲህ እያደረገ ነው ብሎ ማውራት ሰውየውን እንድንጠላ ያደርጋል እንጂ የሰራውን ስሕተት እንድንማርበት አያደርግም ።
ከክርክር(argument)  አንጻርም ስናየው  የተሳሳተ ክርክር ነው ( fallacies )  በሆነ ክርክር ውስጥ ጉዳዩን ሳይሆን ግለሰቡ እንዲህ ስለሆነ እኔ እምለው ትክክል ነው ብሎ እንድመከራከር ነው ። (attacking the person/argument against the man) እሚባለው fallacies ማለት ነው ።
2፦ ስድቦች የተቀላቀሉበት ጽሁፍ መሆኑ ።
“የግሪሳው ቡድን”   “ፓስተር …. ( እዚህ ላይ ፓስተር በራሱ ስድብ ሆኖ ሳይሆን ያለቦታው ሲገባ ግን ሌላ ሽሙጥን ይይዛል።)”   “የበጌ ቡድን”(መቸም መምህሩ በጋሻውን ለማቆላመጥ እንዲህ  እንዳላ ከጽሆፎቹ መገመት እሚከብድ አይደለም) “መናፍቁ …. ግብረ ሰዶማዊ መሆኑ።(መምህራችን ከስድቡም ጀርባ እየነገረን ያለውን እናስተውለው ።)  “ዶላር ወዳለበት እየቶንጦለጦለ ”     “ ግሪሳው የአዕምሮም የገንዘብም ደሃ ነው።”      እያለ ስድብን እያስተማረን ይቀጥላል ።

3፦ሁሉንም ነገሮች ወደ ተሳሳተው መስመር (negative) ጎኑ ብቻ እንዲመራ እሚያደርግ ጽሁፍ መሆኑ።
“የእመቤታችን ስዕል መጥቶ ከእግሬ በታች ይቀመጥ እሷን እያሳየን ስል እርሷ ሳናወራ መመርያችን እንፈጽማለን በማለት …. የእመቤታችን ስዕል ከአትሮኖሱ ከፓስተሩ እግር ስር እንድትቀመጥ ፈርዶባታል።”  
አንዳንዴ አንድን ሰው ወይም ቡድን በአንድ መልኩ ከገመገምነው ወይም ቦታ ከሰጠነው በኋላ ምንም አይነት መልካም ጎን አይታየንም። የትም ቦታ ላይ መንም አይነት ሰዕለ አድኅኖ ከ አትሮንስ ስር ተቀምጦ ተመልክተነዋል ። ነገር ግን በሰው ጭንቅላት ዘንድ መጥፎ ብቻ መጥፎ ጎን ብቻ እንዲታይ የሚያደርግ ጽሁፍ ነው ።
4፦ መምህራችን ፍጹም ትክክል ናቸው መስሚያቸው ጥጥ ነው ።
በጣም ባልጠበኩት ሑኔታ ወደ ጽሁፉ መጨረሻ እየተቃረብን ስንመጣ እንዲህ ይለናል  መምህራችን “ በእኔ በኩል መስሚያየ ጥጥ ነው … ተመልከቱ እንግዲህ ምድረ መናፍቅ ሁሉ ሲንጫጫ ። አልሰማችሁም ምድረ ግሪሳ ሁላ ተንጫጩ እንግዲህ ከያላችሁበት ።”  
የጽሁፉ ዓላማ መናፍቃንን ማንጫጫት ነው ጥቅሙስ ምንድን ነው የነሱ መንጫጫት ተመልስው መዳናቸው ?  ይህንን በመጻፍህስ ማንን ነው ወደ ድኅነት መስመር እምትመራው ?  በእውነቱ መናፍቅ ያልካቸውን በቻ ሳይሆን እኛንም አንጫጭተህናል ።     
እኔ ትክክል  ነኝ ብሎ እሚያምን ሰው ማንንም ለመስማት ዝግጁ አይደለም ። እርሱ ሑሌም ትክክል ነዋ ። መምህር ሆይ አንተስ እንደዛ ማሰብ ጀመርክ እንዴ     “ አንተ በሌላው ሎሌ እምትፈርድ ማን ነህ???” ሮሜ 14፥4  እስኪ ወደ እራህ ለመመልከት ሞክር ደግሞም ወደ ሰው ከተመለከት ለራስህ አድርገው ለሰው ስህተቱ እና አስተምሕሮውን መቃወም ማሳየት ይበቃል ።
ሁሌም ደግሞ ለመስማት የተዘገጀህ ሁን   ሰወችስ ገደል የገቡት ባለመስማታቸው አይደል ። ተቃውሞሕንም ለይልን ሰወችን ወይስ …
“በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ይሰደባል ።” ሮሜ 2፥24  እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ  በየ ሶሻል ሚድያው በመሰዳደብ ክርስትያን ተብለን የእግዚአብሔርን ስም በአሕዛብ ዘንድ አናስነሳ ።
በአጠቃላይ መመህር ሆይ ካንተ ባላውቅ 
Ø  እነርሱ ቢመለሱ እንዲመለሱ አስተምር ።
Ø  ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን መገፈታተርን ሳይሆን ወደመንግስቱ ተያይዞ መግባትን ስበክ
Ø  ባይመለሱ ትክክልም ነን ቢሉ ግን እነርሱን ለፈራጁ ትተህ ወደ አስተምህሮትህ ተመለስ ሁሉንም መዝኖ ሊቀጣ የተዘጋጀ አምላክ አለና ።
Ø  ሁሌም እራን ትክክል ነኝ ብሎ ከማብ ተላቀህ ሰወችን ለመስማት የተዘጋጀህ ሁን ።
Ø  ለምዕመናን እሚነገሩ እና እማይነገሩ መረጃወችን ለይ

። “ ሐዋርያት ነን የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንደዳገኘሀቸው አውቃለሁ …. ስለ ስሜ ብለሕ ጸንተህ አልደከምክም ዳሩ ግን የምነቅፍብሕ ነገር አለኝ።”ረዕ 2፥2
በመጨረሻም አንድ መጽሐፍ እንድታነቡ  ልጋብዝ መድሎተ ጽድቅ (በትክክል ግለሰቦችን ሳይሆን አስተምሕሮን የሚያስቀምጥ።)  ድንቅ ጽሁፍ ።  በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ) ።
ከተሳሰትኩ እታረማለሁ ።
  

0 አስተያቶች:

Post a Comment

Facebook Twitter Addthis Google+